- Explore E-books
- Beauty & personal care
- Books
- Coffee and Tea
- Electronics
- Furniture
- Network Materials
- Office supplies & Services
- Soap and Detergent
- Sports & Tools
Help & Settings
Customer Service
Sign In
Bid Closing Date: ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ክፍት ሆኖ በ11ኛው የሥራ ቀን ጠዋት 4፡00
Bid Opening Date: በ11ኛው የሥራ ቀን ጠዋት 4፡30
Published On: አዲስ ዘመን (Oct 03, 2023)
Bid document price: 300.00 ብር
Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
Region: Addis Ababa
ግልጽ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 የእድገት ጮራ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለቢሮና ለትምህርት አገልግሎት የሚውሉ እቃዎችን ማለትም፤
አድራሻ፡- ከአያት አደባባይ ወደ ጣፎ በሚወስደው መንገድ ገመናዬ ማርያም ቤ/ክ መግቢያ ላይ ይገኛል፡፡
ለበለጠ መረጃ ፡- በስልክ ቁጥር፡- 011 893 2698/011 893 1407
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሚ ኩራ ክ/ከተማ አስተዳደር ት/ጽ/ቤት
የዕድገት ጮራ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
1. ሎት 1. የስፖርት ትጥቅ እና የደንብ ልብስ
2. ሎት 2. አላቂ የቢሮ ዕቃዎች
3. ሎት 3. ህትመት
4. ሎት 4. አላቂ የት/ት እቃዎች
5. ሎት 5. አላቂ የጽዳት እና ሌሎች ዕቃዎች
6. ሎት 6. ሌሎች አላቂ ዕቃዎችና መጻሕፍት
7. ሎት 7. ቋሚ የኤክትሮኒክስ ዕቃዎች
8. ሎት 8. ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች
9. ሎት 9. ለሕንፃ ለቁሳቁስና ለተገጣጣሚዎች እድሳት እና ጥገና
10. ሎት 10. ለፕላን ማሽነሪ እና ለመሣሪያ ዕድሳት እና ጥገና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
የዘመኑን ግብር የከፈሉ ፣ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ፣ በዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር መመዝገባቸውን የሚያረጋጥ ማስረጃ የሚያቀርቡ፣
የገቢዎች እና ጉምሩክ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
አቅራቢዎች ምዝገባ ዝርዝር ማያያዝ የሚችሉ መሆን አለበት፡፡
የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት /ቫት/ የተመዘገበበትን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300/ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ዕድገት ጮራ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
የጨረታው ማስከበሪያ ሎት 6223 ፣ 6219 ፣ 6244 ፣ 6343፡- ለእነዚህ ሎት 3000 ብር እንዲሁም 6211 ፣ 6212 ፣ 6215 ፣ 6313 ፣ 6314 ፣ 6218 ለእነዚህ ሎት 5000 ብር በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ የሚችሉ፡፡
የመወዳደሪያ ዋጋውን ከነቫት በማስቀመጥ በግልጽ ተጠቅሶ መጻፍ ይኖርበታል፡፡
የጨረታው ተሳታፊዎች የሚያቀርቡትን የጨረታ ሰነድ ፋይናንሻል እና ቴክኒካል ዋናውንና ኮፒ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪም የሚወዳደሩበት ዕቃ ናሙና /specification/ ማቅረብ አለባቸው ፡፡ አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው ከታወቀ በኋላ በ15 ቀናት ውስጥ ከት/ቤቱ ጋር ውል መዋዋል አለባቸው፡፡
ተጫራቾች ያሸነፉበትን ደረጃቸውን የጠበቁ ዕቃዎችን ትዕዛዙ በደረሳቸው በአምስት የሥራ ቀናት ውስጥ በናሙናው መሰረት አጠናቀው ለት/ቤቱ ንብረት ክፍል ሲያስረክቡና በጥራት ኮሚቴ ተፈትሾ ሲያልፍና በተቋሙ ኃላፊ ገቢ እንዲሆን ከታዘዘ በኋላ ይከፈላቸዋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ክፍት ሆኖ በ11ኛው የሥራ ቀን ጠዋት 4፡00 የጨረታው ሳጥን ይታሸግና በዚያው እለት በ4፡30 ሰዓት ዕድገት ጮራ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ፋ/ግ/ንብ/አሥ/የቡድን መሪ ቢሮ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
የጨረታው አሸናፊ የጨረታው ውጤት ሲታወቅ የውል ማስከበሪያ ካሸነፈበት ጠቅላላ የጨረታ ዋጋ 10% በጥሬ ገንዘብ CPO በቅድሚያ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የዕድገት ጮራ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሚ ኩራ ክ/ከተማ አስተዳደር ት/ጽ/ቤት
የዕድገት ጮራ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
| Address | ከአያት አደባባይ ወደ ጣፎ በሚወስደው መንገድ ክብር ዳመና አካባቢ ይገኛ |
|---|
Merkatomarket.com
Merkatomarket is your go-to online marketplace for all your needs. We provide a wide range of products with the best deals and customer service.
© 2026 merkatomarket.com. All rights reserved.
powered by BET SOFTNETS