- Explore E-books
- Beauty & personal care
- Books
- Coffee and Tea
- Electronics
- Furniture
- Network Materials
- Office supplies & Services
- Soap and Detergent
- Sports & Tools
Help & Settings
Customer Service
Sign In
Bid Closing Date: ለ21 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቆይቶ በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 3:30 ሰዓት ላይ
Bid Opening Date: በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30
Published On: አዲስ ዘመን (Sep 26, 2023)
Bid document price: 300.00 ብር
Bid bond: 30,000.00 ብር
Region: Sidama
አላቂ የቢሮ የጽ/መሳሪያ ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
1. በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የአለታ ወንዶ ከተማ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት በ2016 በጀት ዓመት አላቂ የቢሮ የጽሕፈት መሳሪያዎችን በጨረታ ዋጋ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ተጫራቾች፡
-አግባብነት ያለው ህጋዊ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያለው/ያላት ኦርጅናል ፎቶ ኮፒ አያይዞ ማቅረብ የሚችል።
-የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው እና የዘመኑን ወይም 2016 ዓ.ም ግብር የገበሩበት ማረጋገጫ ያለው/ያላት ኦሪጅናል ፎቶ ኮፒ አያይዞ ማቅረብ የሚችል፡፡
-የ2015 ዓ.ም የግብር ክሊራንስ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል/የምትችል፡፡
-የቫት ተመዝጋቢ የሆነ እና በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ያለው/ያላት ኦሪጅናል ፎቶ ኮፒ አያይዞ ማቅረብ የሚችል፡፡
-ጊዜው ያላለፈበት በአቅራቢነት በጨረታ ላይ እንዲሳተፉ ከመንግስት መ/ቤት የተሠጠ ማረጋጫ ሰርተፊኬት ያለው/ያላት ኦሪጅናል ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችል፡፡ የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ ብር 30,000 ከታወቀ ባንክ /CPO/ማስያዝ የሚችል፡፡
-የውል አፈፃፀም ዋስትና ማስከበሪያ ከሚያቀርበው ጠቅላላ ዋጋ 10% በጥሬ ወይም ከታወቀ ባንክ የተሰጠ /CPO/ማስያዝ የሚችል።
-ማንኛውንም ወጪዎች ማለትም የጉምሩክ ፤ የትራንስፖርት ፤ የባንክ እና የሌሎች አገልግሎት ወጪዎችን በራሱ ሸፍኖ ዕቃውን ማሰረከብ የሚችል።
-ተጫራቾች የሚጫረቱባቸውን ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡ በጨረታው ተሸናፊ የሆኑ ድርጅቶች ያቀረቡት ናሙና ወዲያው ተመላሽ ይደረጋል።
-ተጫራች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300/ሶስት መቶ ብር/ ለአ/ወ/ከ/ዝ/ባ/ቅ/ጽ/ቤት በመክፈል እና ሰነዱን ከ//ወ/ከ/ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግዥ ሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 08 በመውሰድ በተዘጋጀው የጨረታ ሠነዱ ላይ የአንዱን ዋጋ ብቻ በመሙላት ቴከኒካል ዶከመንት እና ፋይናንሻል ኦርጅናል እንዲሁም ሁለት ሁለት ፎቶ ኮፒው ለየብቻ በማድረግ በአንድ ፖስታ አሽጎ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በ/አ/ወ/ከ/ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግቢ ውስጥ ባለው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን የጨረታ ሳጥን በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 3:30 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
ማሳሰቢያ፡
-ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ለመግዛት ሲመጡ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ኮፒና ማልከቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
-መ/ቤቱ በጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
-አንደ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ሌላው ተጫራች ተንተርሶ መጫረት አይችልም፡፡
-የወቅቱን የገበያ ዋጋ ያላገናዘበ የጨረታ ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውም ከቀረበም የዋጋ ትንታኔ መያያዝ አለበት፡፡
-የጨረታው መክፈቻ ቀን በሥራ ቀን ካልዋለ በቀጣይ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ይሆናል፡፡
-ተጨማር መረጃ ከፈለጉ 046 224 0152 እና 046 224 0627 ደውለው ማረጋገጥ ይችላሉ፡፡
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የአለታ ወንዶ ከተማ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት
Aleta Wondo City Administration Finance and Economic Development Office አለታ ወንዶ ከተማ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት
| Phone | +251 46 224 0627 |
|---|
Merkatomarket.com
Merkatomarket is your go-to online marketplace for all your needs. We provide a wide range of products with the best deals and customer service.
© 2026 merkatomarket.com. All rights reserved.
powered by BET SOFTNETS