- Explore E-books
- Beauty & personal care
- Books
- Coffee and Tea
- Electronics
- Furniture
- Network Materials
- Office supplies & Services
- Soap and Detergent
- Sports & Tools
Help & Settings
Customer Service
Sign In
Bid Closing Date: ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 (አሰራ አምስት ) ተከታታይ ቀናት በ16ኛዉ ቀን በ6፡00 ሰዓት
Bid Opening Date: በ16ኛዉ ቀን በ8፡30
Published On: አዲስ ዘመን (Sep 28, 2023)
Bid document price: 300.00 ብር
Bid bond: 1%
Region: Sidama
የጨረታ ማስታወቂያ
የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን በተለያዩ የመንገድ ግንባታ/ጥገና ፕሮጀክቶች ላይ ጠጠር የሚያመላልሱ ገልባጭ መኪኖች እስከነ ሎደሩ አቅራቢዎችን ከዚህ በታች በተገለጸው መሠረት መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የፕሮጀክቱ ስም |
በክልሉ ውስጥ መንገዱ የሚገኝበት ወረዳ |
የመንገዱ ርዝመት በኪ/ሜ |
አማካይ የምልልስ ርቀት በኪ/ሜ |
|
1 |
ጠጢቻ ቡርሳ ያዬ |
ጠጢቻ-ቡርሳ-አርቦጎና |
11 |
13.5 |
|
2 |
ለኩ ጎርቼ |
ሸበዲኖ -ጎርቼ |
8 |
12 |
|
3 |
መጆ ግርጃ |
አሮሬሳ-ሆኮ |
8 |
7 |
|
4 |
አባዬ ወተራ ጋንዶ ጉጉማ |
ወ/ገነት |
6 |
10 |
|
5 |
ቃባዶ አበራ ሁላ |
ዳራ-ሁላ |
10 |
10.5 |
|
6 |
አንፋራራ ቦኮላ |
ሸበዲኖ |
6.5 |
6.25 |
|
7 |
ጎንዶሮ ሚቂቾ |
አርቤጎና |
34.2 |
36 |
በዚሁ መሠረት -
1. የኮንስትራክሽን መሣሪያዎች የማከራየት ፍቃድ ያላቸው ወይም በጠቅላላ ሥራ ተቋራጭነት ከደረጃ 5 እና ከዚያ በላይ ፍቃድ ያላቸው ሆነው በመንገድ ሥራ ላይ ከዚህ በፊት የሠሩበት የሥራ ልምድ ያለቸው፣
2. ገልባጭ መኪና እስከነ ሎደር የስሪት ዘመን እ.አ.አ 2010 እና ከዚያ በላይ ሆኖ፣ የተሸከርካሪ የመጫን አቅም=14m3 የሆነ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
3. ተጫራቾች አግባብነት ያለው ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስከር ወረቀት፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሠርተፊኬት፣ የግብር ከፋይ ሰርተፊኬት እና በጨረታ መወዳደር የሚያስችል የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ታክስ ክሊራንስ እንዲሁም ከመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መመዝገባቸውን የሚያሳይ ሰርተፊኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
4. ከሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን ጋር ውለታ ገብቶ በአፈጻጸም ችግር ምከንያት ማስጠንቅቂያ ተሰቶት ስራውን ያላጠናቀቄና ውሉ የተቋረጠ የገልባጭ መኪና አከራይ ድርጅት የጨረታ ሰነዱን መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችልም።
5. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 (አሰራ አምስት ) ተከታታይ ቀናት ከባለሥልጣኑ /ቤት ግዥ የፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮቁ ጥር -5 ቀርበው መግዛት ይችላሉ።
6. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ(CPO) ወይም ከታወቀ ባንክ የቀረበ የጨረታ ማስከበሪያ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና (unconditional Bid Bond) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በተጫራቾች የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 1% ማስያዝ ያለባቸው ሲሆን ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ከላይ በተገለጸው መሠረት ይሆናል። ከባንክ የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ለ180 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል።
7. የጨረታ ሰነዱ በተጫራቾች መመርያ መሠረት ተሞልቶ ጨረታ ማሰከበርያ /Bid Security/፣ ፋይናሻል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እናሁለት ኮፒዎችን እንድሁም ቴክኒካል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እናሁለት ኮፒ ሰነዶች በተለያየ ፖስታ በሰም በማሸግ ለየብቻቸዉ ታሽጎ በአንድ እናት ፖስታ ዉስጥ ተካተዉና በሁሉም ዶhመንት ላይ ስምና አድራሻ በመጻፍ ህጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛዉ ቀን ከጧቱ 4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት በሲዳማ መንገዶች ባለሥልጣን በግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይረክቶሬት ክፍል ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያው ከቴክኒካል ሠነድ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት፡፡ ሆኖም የተጠቀሰው ቀን የእረፍት ወይም የህዝብ በዓል ቀን ሆኖ ከዋለ በቀጣይ በስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡
8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወከሎቻቸው በተገኙበት ከላይ የጨረታ መከፈቻ ተብሎ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ በባለስልጣኑ መ/ቤት አደራሽ ይከፈታል፡፡
ማሳሰብያ፡- ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር፡- 046 212 8446
የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን
ሐዋሳ
Sidama Roads Authority ሲዳማ መንገዶች ባለሥልጣን
Sidama Roads Authority ሲዳማ መንገዶች ባለሥልጣን
|
Merkatomarket.com
Merkatomarket is your go-to online marketplace for all your needs. We provide a wide range of products with the best deals and customer service.
© 2026 merkatomarket.com. All rights reserved.
powered by BET SOFTNETS